ጷግሜ 3 ቀን 2014 ዓ.ም
ትምራን ከ ኢትዮጵያ ሴት ማህበራት ቅንጅት፣ ከSIHA Network እና ከአዲስ አበባ ሴቶች ማህበር ጋር በመተባበር የሴቶች የሰላም የእግር ጉዞ በአዲስ አበባ አዘጋጅታለች። በእግር ጉዞው ከ400 በላይ ሴቶች የተሳተፋ ሲሆን መጪው አዲስ አመት የሰላም እንዲሆን ምኞታቸውን ገልፀዋል። በተጨማሪም በሀገራችን ኢትዮጵያ በሚካሄዱ የሰላም ግንባታ ተግባራት ውስጥ ሴቶች ተሳታፊ የሚሆኑበት መንገድ እንዲመቻች ጠይቀዋል። ለዚህ የተሳካ ዝግጅት በአጋረነት ከጎናችን ለነበራችሁ ድርጅቶች እና የፕሮገራሙ ድምቀት ዋንኛ ምክንያት የነበራችሁ ተሳታፊዎችን ሁሉ በትምራን እና ድምፃቸው ባልተሰማ የኢትዮጵያ ሴቶች ስም ከልብ እናመሰግናለን ኑሩልን፡፡