
የጥምረት ለሴቶች ድምፅ በአገራዊ ምክክር መድረክ የተግባቦት ስትራቴጂ እና የአባልነት መመሪያ ረቂቅ ሰነድ ላይ በትምራን አስተባባሪነት ጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም የግማሽ ቀን ውይይት ተካሄደ።
በውይይቱ መክፈቻ ላይ የትምራን ሥራ አስኪያጅ ኢየሩሳሌም ሰሎሞን ስለ ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በአገራዊ ምክክር መድረክ ራእይ እንዲሁም ጥምረቱ እያከናወናቸው ስለሚገኙ ተግባራት አጭር ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የጥምረቱን የተግባቦት ስትራቴጂ እና የጥምረት ለሴቶች ድምፅ አባልነት መመሪያ ሰነድ ያዘጋጁት አማካሪዎች ያዘጋጁትን ረቂቅ ሰነድ ለተሰብሳቢዎቹ በቅደም ተከተል አቅርበዋል።
በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩት የጥምረት ለሴቶች ድምፅ አባል ማኅበራት መካከል የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት ፣ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ ሴቶች ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተከላካይ ማእከል፣ ተርካንፊ ሴቶች ማህበር እና ትምራን እንዲሁም የናሽናል ዴሞክራቲክ ኢንስቲትዩት እና አይሪሽ ኤይድ ተወካዮች የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች አንሥተዋል።
በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ የሰነዶቹ ዝግጅት አማካሪዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ አስተያየቶችን ደግሞ ለሰነዶቹ መዳበር አስፈላጊ በመሆናቸው በግብአትነት እንደሚወስዱ ገልጸው ውይይቱ ተጠናቅቋል።
A validation workshop conducted on the Coalition of Women’s Voice in the National Dialogue draft Communication Strategy and Membership Guidelines
TIMRAN organized a half day validation workshop on the Coalition of Women’s Voice in the National Dialogue (CWVND) draft Communication Strategy and Membership Guidelines on February 02, 2023.
At the workshop opening TIMRAN’s Executive Directress, Eyerusalem Solomon briefed the participants about the vision of the Coalition of Women’s Voice in the National Dialogue and the activities done by its secretariat office, TIMRAN.
The Communication and Advocacy Strategy document preparation and the Membership guidelines document preparation consultants presented the draft documents respectively.
Different questions and suggestions were raised by the participants which include CWVND members like the Network of Ethiopian Women Association (NEWA), Ethiopian Women Lawyers Association (EWLA), Ethiopian Human Rights Defenders Center (EHRDC), Terkanfi Sustainable Development (TSD) and TIMRAN as well as donors NDI and IRISH AID.
The consultants respond to the questions raised and accept the suggestions as input to develop the draft documents at their hand. Following this, the half-day workshop becomes concluded.

