Skip to content

የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ የአርአያ ሴቶች የልምድ ልውውጥ አካሄደ

የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ ከትምራን፣ ከኢትዮጵያ ሕግ ባለሞያ ሴቶች ማኅበር እና ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኅን ሴቶች ማኅበር ጋር በመተባበር የአርአያ ሴቶች የልምድ ልውውጥ መድረክ መጋቢት 02 ቀን 2015 ዓ.ም በዋሽንግተን ሆቴል አካሄደ።

የልምድ ልውውጥ መድረኩ በየዓመቱ የካቲት 29 ቀን (March 08) የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በማስመልከት የተዘጋጀ ሲሆን፣ የኔዘርላንድስ የመልቲፓርቲ ዴሞክራሲ ኢንስቲትዩት እና የአውሮፓ ኅብረት ድጋፍ አድርገዋል።

የኅብረት ለምርጫ ዋና ዳይሬክተር አቶ አበራ ኃይለማርያም ለተሳታፊዎች የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ኅብረት ለምርጫ የሴቶችን የምርጫ ተሳትፎ ለማሳደግ የሦስት ዓመታት ፕሮጀክት ቀርፆ በመተግበር ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት ኅብረት ለምርጫ የአርአያ ሴቶች የልምድ ልውውጥ መድረክ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሴቶች ላይ የተጠኑ ጥናቶችን በመምረጥ አሳትሞ ማሰራጨት፣ ለሴቶች ሥልጠና ማዘጋጀት፣ የአርአያ ሴቶችን ታሪክ አሳትሞ ማሰራጨት፣ የመገናኛ ብዙኀን  ዝግጅት እና ቅስቀሳ ተግባራት እንደሚያከናውን ተናግረዋል።

የዕለቱ መድረክ በተለያየ የሥራ መስክ ተሰማርተው የውሳኔ ሰጭነት ደረጃ የደረሱ ሴቶችን በአርአያነት በማቅረብ ወጣት ሴቶች እንዲማሩ የሚደረግበት መሆኑን አመልክተዋል።

በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሕፃናት እና ሴቶች መብቶች ኮሚሽነር እና የትምራን ቦርድ ሰብሳቢ መስከረም ገስጥ፣ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሐና አርአያሥላሴ እና በአየርላንድ ኤምባሲ ከፍተኛ የአስተዳደር ሓላፊ እና የትምራን ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ብሌን አሥራት የሕይወት ተሞክሮአቸውን ለተሳታፊ ወጣቶች አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *