Skip to content

አዎንታዊ ሰላም

አዎንታዊ ሰላም

ኖርዌጂያዊው ግንባር ቀደም የሰላም ጉዳይ ተመራማሪ ጆሃን ጋልቱንግ ሰላም ሁለት ዓይነት ገጽታ እንዳለው ይገልጻል።

የመጀመሪያውን ተቃርኖአዊ ሰላም ይለዋል። ይኽም ጦርነት እና ብጥብጥ የሌለበት፣ ነገር ግን ኅብረተሰቡ የመረጋጋት እና የስምምነት ችግር በሚታይበት ጊዜ ያለ የሰላም ዓይነት ነው።

ሁለተኛው አዎንታዊ ሰላም ነው። ይኽ ዓይነቱ ሰላም ዘላቂነት ያለው፣ ለኢኮኖሚያዊ ልማት እና ተቋማት ግንባታ የሚረዱ አስተማማኝ ኢንቨስትመንቶች የሚታዩበት እንዲሁም ኅብረተሰቡ የሰላም ግንባታን ለማፋጠን የሚያስችል አመለካከት ያለው መሆኑ የሚገለጽበት ነው። ይኽም ኅብረተሰቡ ሰላምን ለማጽናት ያለው አቅም የሚለካበት ወይም ፈተናዎች ቢያጋጥሙ ያለ ችግር አልያም ወደ ግጭት ሳይገባ የመቋቋም ችሎታው የሚለካበት ነው።

አዎንታዊ ሰላም ‘የብጥብጥ መዋቅሮችንና ልማዶችን’ ይቃወማል። እነዚህ መዋቅሮች እና ልማዶች ሰዎች ወደ ኃይል አማራጭ እንዲገቡ አልያም በሌሎች ላይ ሁከት እንዲፈጽሙ ያደርጋሉ።

በመሆኑም አዎንታዊ ሰላም ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቀባይነት እያገኘ፣ በምሁራን እና በፖለቲከኞች ዘንድ በስፋት አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል።

ባለፉት 2500 ዓመታት ውስጥ ‘ሰላም’ የሚለው ፅንሰ ሐሳብ ትርጓሜ በየጊዜው እየተሻሻለ መጥቷል። በዚህም መሠረት የጦርነት ምክንያቶች ላይ ከማተኮር ይልቅ ሰላማዊ ዓለም ለመፍጠር የሚያስችሉ አመለካከቶች፣ ተቋማት እና መዋቅሮችን መፈተሽ እና በሁሉም አካባቢዎች እነዚህ ሁኔታዎች እንዲሟሉ ትኩረት በመሰጠት ላይ ይገኛል። 

ለአብነት በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ባሕሎች የሰላምን ፅንሰ ሐሳብ የሚገልጹበትን አግባብ መመልከት ይቻላል።

ሕንዳውያን በጉዳት ወይም ግጭት ውስጥ ሆነው እንኳን የአእምሮ መረጋጋትን ለመጠበቅ ’ሻንቲ’ የሚል ሐሳብ ይጠቀማሉ።

ጃፓናውያን ደግሞ ራስን ከማኅበረሰባዊ ሥርዓት ወይም የጋራ መልካም እሴት ጋር ማስተሳሰር ወይም ‘ሄይዋ’ የሚባል ባሕል አላቸው።

አይዳውያን እንዲሁ መልካም መስተጋብር ወይም አንድነት እና ብልጽግና፣ ከፍትሕ የመነጨ ለሁሉም ማሰብን የሚገልጽ ‘ሻሎም’ የሚል ተግባራዊ ሐሳብ ያራምዳሉ።

ደቡብ አፍሪካውያኑ ዙሉዎች በበኩላቸው ከሰብአዊነት ጋር የተሳሰረ የራስ ዋስትና መኖር፣ የምሉዕ አንድ አካል  መሆን ወይም ‘ኡቡንቱ’ የሚል እሳቤ ይተገብራሉ።

ከእነዚህ በርካታ እሳቤዎች ውስጥ የሚወለደው አዎንታዊ ሰላም ስልታዊ እና ውስብስብ፣ ሞራላዊ፣ ተከላካይ፣ በጽናት ላይ የተመሠረተ እና ብጥብጥ አልባ፣ መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ገጽታ ያለው እንዲሁም የልማት ግቦችን የሚደግፍ መሆኑን positivepeace.org ድረ ገጽ ላይ የወጣ መረጃ ይገልጻል።

በሌላ በኩል World Peace Index ላይ የወጣ መረጃ የሚከተሉት ጉዳዮች ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን እንደሚወስኑ ያመለክታል። ከፍ ያለ የአዎንታዊ ሰላም ደረጃ መድረስ ከፍተኛ ገቢ፣ የተሻለ አካባቢያዊ ውጤቶች፣ ከፍተኛ የኑሮ ሁኔታ፣ ከፍ ያለ የልማት ውጤቶች እና ከፍተኛ ችግርን የመቋቋም ብቃት መኖሩን እንደሚያሳይ ይተነትናል።

የአዎንታዊ ሰላም መኖር አንድ ማኅበረሰብ ችግርን የመቋቋም ብቃት ያለው ስለመሆኑ መለኪያ ተደርጎ ይወሰዳል፤ ይህም ዜጎችን ከፈተናዎች የመጠበቅ ችሎታ እና ችግር ባጋጠመ ማግስት የማኅበረ-ኢኮኖሚው ሥርዓት መልሶ እንዲያገግም የማድረግ አቅምን ያመለክታል።

ሀገራችን ኢትዮጵያም የሺህዎች ዓመታት የመንግሥት ታሪክ ሂደት ውስጥ በኅብረ ብሔራዊነት እና ኅብረ ባሕሎች መካከል ተባብሮ እና ተከባብሮ የመኖር አኩሪ ታሪክ አላት።

እንደ ሀገር ይህ አንዱ የአዎንታዊ ሰላም መገለጫ ነው፤ በመሆኑም ብዙ ፈተናዎች ቢኖሩብንም ሁላችንም ለሰላማችን ዘብ ልንቆም ብሎም ያሉንን በጎ እሴቶች ጠብቀን ለትውልድ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል።

POSITIVE PEACE

The Norwegian pioneer of peace research Johan Galtung distinguished two types of peace.

Negative peace: is the absence of war and violence and it does not capture a society’s tendencies toward stability and harmony.

Positive peace: defined by a more lasting peace that is built on sustainable investments in economic development and institutions as well as societal attitudes that foster peace. It can be used to gauge the resilience of a society, or its ability to absorb shocks without falling or relapsing into conflict.

Positive Peace opposes what is known as the ‘structures and cultures of violence’. These structures and cultures can cause people to behave violently, or impose violence on others.

This definition has since increased in popularity and is now widely used by academics and politicians alike.

Our understanding of the term ‘peace’ has evolved significantly over the last 2,500 years.

Instead of looking at the causes of war, we can explore the attitudes, institutions, and structures that build a more peaceful world, and strive to create these conditions in all areas.

Most cultures explore the concept of peace:

Shanti (Indian; to maintain a tranquil mindset even in suffering or conflict)

Heiwa (Japanese; aligning oneself to the common good/social order)

Shalom (Hebrew; right relationships or unity and prosperity, a sense of wholeness arising out of justice)

Ubuntu (Zulu; self-assurance through linked humanity, one part of a whole)

Through these several dimensions of positive peace emerge:-

  • Systemic and complex
  • Virtuous or vicious
  • Preventative
  • Underpins resilience and nonviolence
  • Informal and formal
  • Supports development goals (positivepeace.org)

The info taken from the World Peace Index indicates the following factors lead to many other desirable socio-economic outcomes. Higher levels of Positive Peace are statistically linked to greater income growth, better environmental outcomes, higher levels of well-being, superior developmental outcomes, and stronger resilience. Positive Peace is a gauge for societal resilience, or the ability to shield its citizens from shocks and to promote the recovery of the socio-economic system in their aftermath.

Ethiopia has an honored history of thousands of years of governmental administration within multinationalism and multiculturalism which is manifested by collaboration and peaceful coexistence.

As a nation this is one of the manifestations of a positive peace; though we face many challenges we have to stand firm for the cause of our peace and keep our good values as well as the responsibility to transfer to the coming generation.    

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *