ትምራን በተመድ የሴቶች ዘርፍ የምሥራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ከሆኑት ዘቢብ ካዙማ እና የተመድ የሴቶች ዘርፍ አ.አ ልኡካን ቡድንን ታኅሣሥ 11 ቀን 2015 ዓ.ም በቢሮዋ ተቀበለች።
ሁለቱ ወገኖች ጋር በሴቶች ጉዳይ ላይ ያተኮሩ በርካታ ሃሳቦች በማንሣት ውይይት አድርገዋል፤ የሴቶችን አቅም ለመገንባት በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል።
ትምራን ኢትዮጵያውያን ሴቶች የሚያራምዱት የትኛውም የፖለቲካ አመለካከት ወይም ፓርቲ አባልነት ሳይገድባቸው በሀገሪቱ የፖለቲካ እና ውሳኔ ሰጭነት ላይ ያላቸው ተሳትፎ እንዲጨምር ለማድረግ የምትሠራ ወገንተኛ ያልሆነች በሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ኤጀንሲ መጋቢት 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተመዝግባ የምትንቀሳቀስ ሀገር በቀል ሲቪል ማኅበር ነች።
ትምራን በሀገሪቱ የፖለቲካ ተሳትፎ ውስጥ ያለው የጾታ ኢ-ፍትሐዊነት እንዲጠብ ለማስቻል ራእይ በሰነቁ ዘጠኝ ኢትዮጵያውያን የተመሠረተች ማኅበር ነች።
የተመድ የሴቶች ዘርፍ ድርጅት የጾታ እኩልነትን ለማስፈን እና የሴቶችን አቅም ለመገንባት የተቋቋመ ዓለም አቀፍ ድርጅት ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሴቶች እና ልጃገረዶችን ፍላጎቶች እውን ለማድረግ ተግቶ ይሠራል።